.png)
" ትናንት ፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና ! "
ኢትዮጵያ በህብር የደመቀች ፣ በታሪክ የገዘፈች ፣ በመደመር ትውልድ ተስፋዋን ያለመለመች ሀገር ናት።
የሀገራችንን የመረዳዳት ፣ የመተሳሰብ ፣ የአብሮነት እሴቶች ለማጎልበት እና ህብረ ብሔራዊ አንድነቷን ለማጠናከር ደግሞ ኪነ ጥበብ ጉልህ ድርሻ ትጫወታለች ፤ ተጫውታለችም።
አዲስ አበባን ውብ አበባ በማድረግ የብልፅግና ተምሳሌት እንድትሆን የተጀመረው ርብርብ ደግሞ ለኪነ ጥበብ ማንሰራራት ትልቅ ዕድል ይዞ መጥቷል።
ከመጋቢት እስከ መጋቢት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በየዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን የሚዘክር ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት በአሰባሳቢው የአድዋ ድል መታሰቢያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች በተገኙብነት " ትናንት ፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና ! " በሚል ርዕስ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሂዷል።
የሀገራችን ሉዓላዊነት ተጠብቆ እንዲዘልቅ የህዝባችንን አብሮነት በማጠናከር ኪነጥበብ የድርሻዋን ተወጥታለች።
ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት የመደመር ትውልድ በላቡ ጠብታ ባስመዘገበው ተጨባጭ ልማት እና የሀገርን ህልውና የሚፈታተኑ ተግሮቶችን በድል እንዲወጣም ኪነ ጥበብ አሻራዋን አሳርፋለች ፤
የመጋቢታዊያን ፍሬዎችን ለመዘከር በዛሬው ዕለት በአድዋ ድል መታሰቢያ የተካሄደው ደማቅ የኪነ ጥበብ ድግስም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቀጣይም ለምናደርገው ብርቱ ጥረት የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በአግባቡ በመጠቀም ኪነ ጥበብ ሚናዋን ከፍ እንድታደርግ የሚያግዝ ነው፡፡
ህብረ ብሔራዊ ዜማዎች እና ባህላዊ ውዝዋዜዎች ፕሮግራሙን አድምቀውታል::
የከተማችን ልማት የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽል ፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ የሚያደርግ ፣ አካታች እና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የሚያሳይ ቴአትር በአንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ቀርቧል።
የመጋቢታዊያን ቱሩፋቶችን ለመዘከር በተዘጋጀው ደማቅ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅት ላይ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶችም ድንቅ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
በፕሮግራሙ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሂሩት ካሳው ሌሎችም የስራ ኃላፊዎች ፣ አንጋፋና ታዳጊ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተካፍለዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/ addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.