" ትናንት ፣ ዛሬ እና ነገ ለኢትዮጵያ ልዕልና ! "
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስብራቶች ማብቂያ የተበሰረባት ፣ ኢትዮጵያን የሚያሻግር አዲሱ የመደመር አሳቤ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስቻለው ሀገራዊ ለውጥ ዕውን የሆነባት ፤
ሁለንተናዊ ብልፅግናን በማረጋጥ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ለማብሰር መሰረት የተጣለባት ፤
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለመቆም ተቃርቦበት ከነበረበት የታደገው ሀገራዊ ለውጥ ዕውን የሆነባት ፤
የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት በመረዳት ወደከፍታዋ የሚወስዳትን መንገድ የቀየሱት የዓለም የሰላም ኖቬል ሽልማት አሸናፊው ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡባት ፤
አዲስ አበባን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ቁርጠኛ አቋም የተያዘባት መጋቢት 24 በከተማ ደረጃ በፓናል ውይይት መከበር ጀምሯል።
በፓናል ውይይቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ ምሁራን ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ አባገዳዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.