ባለስልጣኑ በዛሬው ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለስልጣኑ በዛሬው ያልተጣራ ፍሳሽ በመልቀቅ ወንዝን የበከለ ተቋም 1,000,000 ብር መቅጣቱ ገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 10 የፋብሪካ ፍሳሽን ወደ ወንዝን በመልቀቅ ወንዝ የበከለው ተቋም 1,000,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለፀ።

ባለስልጣኑ ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሚለቁት ፍሳሽ በተደረገለት የናሙና ምርመራ ወንዝን የሚበክል መሆኑን የተረጋገጠ ሲሆን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት በገንዘብ ቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዶበታል።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.