የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመዲናዋ የታየዉን የ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመዲናዋ የታየዉን የናፍጣ እጥረት ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ቢሮዉ  በመዲናዋ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ያለውን የናፍጣ እጥረት ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን  አስታዉቋል።

 ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ቀናቶች በከተማዋ ያጋጠመውን የናፍጣ  አቅርቦት እጥረት መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጋር በመሆን በቅርበት እየሰራ መሆኑን  ቢሮዉ አስታዉቋል።

 በዛሬው እለትም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ  አመራሮችንና ባለሙያዎችን በማካተት  ከንግድና ቀጠናዊ ሚኒስቴር  ጋር   የተቀናጀ ሳባት ቡድን አደራጅቶ በሁሉም ማዲያዎች ምልከታ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

 ቢሮዉ በቅንጅት የጀመረዉን ምልከታ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ለችግሩ  አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሶ መረጃዎችን በተከታታይ ለማህበረሰቡ እንደሚያቀርብ ጭምር  አስታውቋል፡፡


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.