.png)
ዛሬ "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ከተማ አቀፍ የኢትዮጵያ - አዲስ አበባ ታምርት የ2017 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ የኢኮኖሚ ልህቀት ማዕከል በሆነው አዲስ ዓለምአቀፍ የኮንቬንሽን ማዕከል አስጀምረናል።
የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቀዳሚ ትኩረት ከተሰጣቸው የኢኮኖሚ መስኮች መካከል አንዱ በመሆኑ አዲስ አበባ ከተማን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ፈጠራን በማበረታት፣ አመራቾችን በመደገፍ፣ ፋይናንስ በማቅረብ፣ የመስሪያ ቦታዎችን በማመቻቸት፣ መሠረተ ልማትን በማሟላት፣ አስፈላጊ ሙያዊ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም ለአመራቾች ድጋፍ በማድረግ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንገኛለን።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዘርፉን ከማነቃቃት ባለፈ በተለያዩ ምክንያቶች ማምርት አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ምርት ስራቸው እንዲመለሱ እንዲሁም አምራቾች ምርታቸውን ለሸማቹ እንዲያስተዋውቁ፣ የገበያ ትስስር አንዲፈጥሩ፣ ሽያጭ እንዲያከናውኑ እና አምራቾች ከፍ ባለ መድረክ ተገኝተው ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያደርግ መድረክ ነው።
የከተማችን ነዋሪዎች ይህን ከ250 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተሳተፉበትን አውደ ርዕይ እንድትጎበኙ እንዲሁም በሀገር ምርት በመጠቀም፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን በመደገፍ እና የሀገር ውስጥ ምርት በመግዛት አምራች እንዱስትሪዎችን እንድታበረታቱ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.