ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ባለፈው አንድ ወር ገደማ የኢትዮጵያን ሕገ መንግሥት፣ የፕሪቶርያን ስምምነት እና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡን ምክር በማከል ሰፊ ውይይቶች ሲካሄዱ ቆይተዋል::

የአቶ ጌታቸው የሥልጣን ዘመን በሕጉ መሠረት ሲያበቃ የሚቀሩ ቁልፍ ሥራዎችን የሚያከናውን አካል፣ ግዝያዊ መንግሥቱ መቀጠለ አለበት የሚል ድምዳሜ ከተያዘ በኋላ፣ ይሄንን ሽግግር ማን መርቶ ከግብ ሊያደርስ ይችላል? የሚሉ ውይይቶችን ስናደርግ ቆይተናል::

ዛሬ በይፋ እና በሰላማዊ መንገድ በአዲስ ባህል የሥልጣን ሽግግሩን እና ቅብብሎሹን ለማካሄድ የተዘጋጀ ፕሮግራም አከናውነናል። ጄኔራል ታደሰ ባለፋት ሁለት ዓመታት የአቶ ጌታቸው ምክትል ሆነው ያገለገሉ ሰው ናችው:: ባለፋት ሁለት ዓመታት የነበሩ ድካሞችን እና ጥንካሬዎችን በግልጽ የሚገነዘቡ ሰው ናቸው:: አሁን ትግራይ ውስጥ ያለውን ክፍተት ሞልተው ወደ ፊት ሊወስዱ ይችላሉ የሚል እምንት በብዙ አካላት የታመነ ነው። የትግራይ ሕዝብ የጠማውን ሰላም እና ልማት፣ እንደ ሌሎች ወንድሞቹ ወጥቶ የመግባት መሻት ስናሳካ፣ ለኢትዮጵያም ለአፍሪካም እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ሠርቶ ለማለፍ ታሪክ የሰጣቸውን ዕድል እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.