
በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በ4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት፤-
1ኛ.በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበዉን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር በመሆን በአካባቢዉ ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት ፣ የምርምር ፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ ፤ ካቢኔዉ ተወያይቶ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ አፅድቋል፡፡
2ኛ.የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል::
3ኛ.የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ካቢኔዉ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡
4ኛ.በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ ካቢኔዉ ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.