"ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ /ቤት በሁሉም ክፍለ ከተሞች የአባላት ኮንፈረስ ጀምሯል።
ኮንፈረንሱ "ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን ባለፉት ቀናት በመሰረታዊ ድርጅት እና በወረዳ ደረጃ ሲካሄድ በነበረው የአባላት ኮንፈረንስ የተመረጡት የመሰረታዊ ድርጅት አመራሮች፣ የህዋሳት አመራሮችና የፓርቲው አባላት በኮንፈረንሱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።
በኮንፍረንሱ በግማሽ ምርጫ ዘመን የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት ፣ በአፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች እና የቀጣይ ትኩረት አቅጣዎች ዙሪያ ውይይት የሚካሄድባቸው ርዕሰ ጉዳዬች ናቸው።
መድረኩም የፊታችን እሁድ በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ከተማ አቀፍ ኮንፈስ የሚሳተፉ ተወካዬቻቸውን ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.