
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካሳንቺስ አካባቢ የንግድ ሱቅ የነበራቸው ነጋዴ የኮሪደር ልማት ተነሺዎች ምትክ የመስሪያ ቦታ በለማው ካዛንቺስ ላይ ተረከቡ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ በቀበሌ ንግድ ቤት ሲሰሩ የነበሩ የልማት ተነሺዎች ግልፅና ይፋዊ በሆነ መልኩ እጣ በማውጣት በዘመናዊ መልኩ የተገነቡ የንግድ ሱቆችን የተረከቡ መሆኑን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አዲሱ ሻንቆ ገልፀዋል።
በዛሬው እለት የንግድ ሱቃቸውን የተረከቡት በጽህፈት መሳሪያ፣ በህንፃ መሳሪያ፣ በመብራት እቃዎች፣ በአገልግሎት ንግድ እና በሌሎች የሙያ መስኮች የተሰማሩ መሆናቸውም ተገልጿል።
በቀጣይም እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ መስሪያ ቦታዎች እየተገነቡ ቀሪ ነጋዴዎችን ፍትሃዊ በሆነ አግባብ በእጣ የማከፋፈሉ ስራ እንደሚቀጥልም ከክፍለ ከተማው ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያስረዳል
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.