የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ የገበያ ት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአምራች ኢንዱስትሪዎች አውደ ርዕይ የገበያ ትስስር በመፍጠር ሚናው ከፍተኛ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የአምራቾችን ምርታማነት ለማሻሻል ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ አምራቾች የነበረባቸውን የመሰረተ ልማት እና የቦታ ችግር በየደረጃው እየፈታ ይገኛል፡፡

  
ከመጋቢት 29/2017 ዓ.ም ጀምሮ “ከሸማችነት ወደ አምራችነት” በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት ከተማ-አቀፍ አውደ ርዕይ በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እያካሄደ ነው።
 
ይህ አውደ ርዕይ አምራች ኢንዱስትሪውን ከሸማቹ ማህበረተሰብ በማገናኘት ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ እና የገበያ ትስስር በመፍጠር ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡

በአውደ ርዕዩ የእንጨት ብረታ ብረት ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ውጤቶች፣ የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብአት ውጤቶች፣ አግሮ ፕሮሰሲንግ እና ፋርማሲቲካል እንዲሁም የቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ውጤቶች በስፋት የቀረቡ ሲሆን አምራቾቸ ምርቶቻቸውን በብዛት እየሸጡ እንደሚገኙ የባዛሩ ተሳታፊ አምራቾች ገልጸዋል፡፡

ሸማቾች በበኩላቸው ኢንደዚህ አይነት አውደ ርዕይ መዘጋጀቱ  የተለያዩ ምርቶቸን  በአንድ ቦታ በተመጣጣኝ ዋጋ እንድናገኝ አስችሎናል ሲሉ  አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ እስከ ሚያዚያ 04/2017 ዓ.ም ድረስ ይቆያል፡፡

የሀገር ዉስጥ ምርቶችን በመግዛት አምራች ኢንዱስትሪዎችን እናበረታታ!


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.