.png)
ህዝብን ማገልገል ኩራት ብቻ ሳይሆን ከኩራትም በላይ ነዉ :-ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
ለ6ኛ ዙር ከ2ሺ በላይ ወንድና ሴት እጩ ሠልጣኝ ፓራሚሊተሪ ኦፊሠሮችን ለማሠልጠን የማስጀመሪያ መክፈቻ ስነስርዓት በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ
ከአዳስ አበባ ከተማ ከ11ዱም ክፍለከተሞች የተመለመሉ ከ2ሺ በላይ እጩ ሠልጣኝ ፓራሚሊተሪ ኦፊሠሮችን በሲዳማ ክልል ይርጋለም ከተማ በሚገኘዉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩንቨርሲቲ አፖስቶ ካምፓስ ለማሰልጠን በዛሬዉ እለት የስልጠና ማስጀመሪያ መክፈቻ ስነስርዓት በደማቅ ሁኔታ ተከናዉኗል።
የአዲስ አበባ ስላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በአስተላለፉት መልዕክት ባለስልጣን ተቋማቱ በከተማችን ከተሰሩ እና ለዉጡ ካመጣቸዉ ትሩፋቶች መካከል አንዱና ዋናዉ የህግ የበላይነትን ለማስፈን በአደረጃጀት በአሰራር እና በቴክኖሎጁ ራሱን በማዘመን የተሠጠዉን ተልዕኮ በተገቢዉ በመወጣት ከተማችን ምቹና ሠላሟ የተጠበቀ እንድትሆን አስችሏታል ብለዋል።
ህዝብን ማገልገል ኩራት ብቻ ሳይሆን ከኩራትም በላይ ነዉ ያሉት ኃላፊዋ ከተማዋን የሚመጥን ተሻጋሪ እመርታዊ ለዉጥ ይበልጥ ለማስመዝገብ አቅም ፈጥራችሁ እንድትወጡ ከ6ኛዉ ዙር ሠልጣኞች የሚጠበቅ ነዉ በማለት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና-ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበኩላቸዉ ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሠጠዉ ስልጣን መሠረት ለ6ኛ ዙር ከ 2ሺ በላይ ፓራሚሊተሪ ኦፊሠሮች ለማሰልጠን ከ11 ክፍለ ከተሞች የመለመላቸዉን ዲግሪና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሠልጣኞችን የአካልና የጤና ምርመራ በማድረግ በምልመላው አልፈዉ ወደ ማስልጠኛ ካምፓስ መግባት መቻላቸዉን ተናግረዋል።
ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመስጠት አስፈላጊ በሆኑ የሎጅስቲክና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን ጠቁመዉ የዛሬዉ የስልጠና ማስጀመሪያ መክፈቻ ስነስርዓትም የዚሁ አንዱ አካል ነዉ ብለዋል።
አክለዉም በስድስተኛ ዙር ለዕጩ የፓራ ሚሊተሪ አዲስ ሰልጣኞች የሚሠጠዉ የንድፈ ሀሳብ እና ወታደራዊ ሥልጠና ከ2 ወር በላይ እንደሚቆይ የጠቀሡት ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የሥልጠና ዓላማዉም በየጊዜዉ ተቋማችን የተለያዪ ደንቦችን አዋጆችን እና መመሪያዎችን በማዉጣት በከተማችን የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ደህንነት ጥበቃን ለማጠናከር እና የሰው ሀይል ክፍተትን ለመሙላት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.