
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ጋር በመሆን የቃሊቲ የሀገር አቋራጭ እና የመካከለኛ ትራንስፖርት መናኻሪያ ግንባታን ጎብኝተዋል::
በ3 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የቃሊቲ የሀገር አቋራጭ እና የመካከለኛ ትራንስፖርት መናኻሪያ ለዋናው መንገድ ቅርብ ሲሆን በሰዓት 120 አውቶቢሶችንና 7ሺ 200 ተሳፋሪዎችን የሚያስተናግድ፣ 4ሺ800 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሁለገብ ህንጻ፣ 13 የትኬት መቁረጫ ቢሮዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ የመመገቢያ ስፍራዎች፣ ከ1ሺ 130 በላይ የማረፊያ ወንበሮች፣ ከ8ሺ ካሬ ሜትር በላይ የአረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም ከጎኑ የታክሲ ተርሚናል የተዘጋጀለት ማዕከል ነው::
የህዝብ ትራንስፖርት ስርዓትን ለማዘመን እየተከናወነ ባለው ተግባር ተሳፋሪዎች በጸሀይ እና በዝናብ ሳይንገላቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መናኻሪያዎችን ለማዘመን በሚሰራው ስራ የአቃቂ መናኻሪያ የኤሌክትሮኒክስ የትኬት መቁረጫ ስርዓትን ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ለሌሎች ሞዴል በሚሆን ደረጃ የተገነባ ነው::
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.