ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ጉዞ የኢን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከሸማችነት ወደ አምራችነት የሚደረገው ጉዞ የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከፍ ለማድረግ ይረዳል - አቶ ጃንጥራር አባይ

ኢትዮጵያ-አዲስ አበባ ታምርት "ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አዘጋጅነት የፓናል ውይይት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ በሚገኘው የፓናል ውይይት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ ባስተላለፉት መልዕክት መድረኩ በዘርፉ የበለጠ ግንዛቤ ለመፍጠር እና የኢንዱስትሪውን ዘርፍ ከፍ ለማድረግ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

"ከሸማችነት ወደ አምራችነት" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው በዚህ መድረክ፣ ዘርፉን የተመለከቱ ሀሳቦች እየቀረቡ ሲሆን የተለያዩ አምራቾች እና ባለድርሻ አካላትም እየተሳተፉ ይገኛሉ።

AMN

 

 

 

 

 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.