ለኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ለኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልፅግና ፓርቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት በፓርቲው የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

‘የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና በእውነት’ በሚል መሪ ሀሳብ የተሰጠው ስልጠና ሲጠናቀቅ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ፤ ስልጠናው ብቁና በእውቀት የጎለበተ ባለሙያ ለማፍራት ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

ዘመኑን የዋጀ የኮሙኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት እውቀትና ግንዛቤ መፍጠር የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ይህ ስልጠና ዘርፉን ለሚመሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የላቀ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የፓርቲው መረጃ አመላክቷል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.