የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ መድረክ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የኢትዮጵያ አዲስ አበባ ታምርት ንቅናቄ መድረክ በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄ ነው

በመርሃግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣አምራቾች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መድረኩ አምራቾች በየደረጃው የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያደርጉበትም  ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ3700 በላይ በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዳሉ እና የነዚህ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማ 64 በመቶ መድረሱን በመድረኩ አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል።

ዘርፉን ለማሻሻል የኢንደስትሪ ፖሊሲ ተቀርጾ  እየተሰራ ነው።  አሁን ላይ በዘርፉ  ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯልም ተብሏል።

የኢትዮጵያ አዲስ ከበባ ታምርት ኤግዚቢሽን እና ባዛር በስኬት እንዲካሄድ ያስቻሉ አካላትንም ም/ከንቲባው አመስግነዋል።

መድረኩን የከተማ አስተዳደሩ የኢንደስትሪ ልማት ቢሮ አዘጋጅቶታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.