ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሀኖይ ቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይም ይሳተፋሉ።

በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል። ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ ጀምሯል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሃይ ኃይል ማመንጫ ምርት ባሻገር የኃይል ማመንጫ ፋብሪካ እንዲያቋቁም አበረታተዋል። ይኽም ሀገራችን ከያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ ጋር የተናበበ በማደግ ላይ ላለው የኃይል ጥያቄም ምላሽ በመስጠት ሊያግዝ የሚችል መሆኑን አውስተዋል።

#PMOEthiopia

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.