
በዚህ ወር አዲሱ የ"Femmes d’Afrique" መጽሔት እትም ደርሷል!
ይህ መጽሄት በወቅታዊ አህጉራዊ ጉዳዮች እና በጠንካራ የአፍሪካ ሴት መሪዎች አስደናቂ ስኬቶች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ፓንአፍሪካዊ መጽሄት ሲሆን በዚህ እትም የሚከተሉትን ርእሰ ጉዳዮች አካቷል
በሽፋን ታሪክ፡-
ባለራእይ ጠንካራ አመራር
የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ ከሆኑት ከወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጋር የተደረገ ልዩ የቃለ መጠይቅ ቆይታ ይኖረናል። ከንቲባዋ የመዲናዋ አስደናቂ የለውጥ ጉዞና የኢትዮጵያ ዋና ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ያላቸው ጽኑ ራዕይ ያጋሩናል!
ማህበረሰብ እና ህዝባዊ ድጋፍ አምድ፤-
የአፍሪካ አህጉር አቀፍ የሴቶች መብት ቀንን አከባበርን በተመለከተ የአንጎላ ምክትል ፕሬዝዳንት ወ/ሮ እስፔራንሳ ዳ ኮስታ፤ የጋቦን ቀዳማዊ እመቤት ወ/ሮ ሴልማ ዚታ ኦሊጊ ንጉኤማ፤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ሮ ቪክቶር ቶሜጋህ-ዶግቤ እና ሌሎች ብዙ አነቃቂ ሴቶችን አካተናል።
በፖለቲካ እና አመራር አምድ ፤-
በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ላይ በተለይም በ29ኛው የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ጉባኤ ላይ ያተኩራል። በጉባኤው የሴራሊዮን ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ፋቲማ ማዳ ባዮ የኦፒዲኤድ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ የአንጎላዋ ወ/ሮ አና ዲያስ ሎሬንሶ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል። እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ውስጥ ታዋቂ ሰዎች ስለሆኑት ስለ ወ/ሮ ሰልማ ማሊካ ሀዳዲ፣ ወ/ሮ አማ ትውም-አሞአ እና ወ/ሮ ሌራቶ ዶሮቲ ማታቦጌ ሽፋን ይሰጣል።
በስፖርት አምድ፡-
ለዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የተመረጡ የመጀመሪያዋ ዚምባቡዌዊት ሴት ክሪስቲ ኮቨንትሪ ተካተዋል።
ይህ የ"Femmes d’Afrique" መጽሔት እትም እንዳያመልጥዎ! አሁን በሞሮኮ የመጀመሪያው ዲጂታል የዜና መስመር በሆነው በካፕሊን እና በአካባቢዎ በሚገኙ የጋዜጣ መሸጫዎች ላይ ይገኛል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.