የተረጋጋና ፍትሐዊ የበዓል ግብይት እንዲኖር በቅ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የተረጋጋና ፍትሐዊ የበዓል ግብይት እንዲኖር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ተገለፀ

የተረጋጋና ፍትሐዊነት የሰፈነበት የፋሲካ በዓል ግብይት እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አስታወቁ።

ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ ይህን የተናገሩት የፋሲካን በዓል አስመልክቶ የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ ውይይት በመሩበት ወቅት ነው።

የበዓል የፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ እስካሁን በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ዝርዝር ሪፖርት በአቶ ተስፋዬ ደንድር የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ ቀርቧል። በዚህም በኮንትሮባንድ፣ በህገ-ወጥ ንግድና አዋኪ ድርጊቶችን በማስገድ ፣እንዲሁም ገበያውን በማረጋጋትና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪን በመከላከል፤ ገበያውን ከደላላ ነጻ ማድረግን አስመልክቶ ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ እንዳሉት የፋሲካ በዓልን አስመልክቶ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር፣ የተረጋጋ ግብይት እንዲኖር ፍትሐዊና ጥራቱን የጠበቀ የምርት ስርጭት እንዲካሄድ ፣ በተጨማሪም ህገ-ወጥነትን በመቆጣጠር እምርታዊ ውጤት እንዲመጣ በቅንጅት ተሰርቷል ብለዋል።

የፍጆታ ምርቶች ያላግባብ በመጋዘን በመከዘን፣ ነዳጅ በማሸሽ፣ የምርት አቅርቦቱን ላይ እጥረት እንዳይፈጠር፣በተጨማሪ በእርድ እንስሳት ላይ ምክንያታዊ ያልሆነ ዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ቁጥጥራችን መጠናከር አለበት ሲሉም አክለዋል።

በተሰጠው የስራ አቅጣጫ መሠረት የበዓል ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር እንዳይቀላቀሉ፣ የሀሰተኛ የብር ኖት ወደ ገበያ እንዳይገባ በጥንቃቄ መስራት ያስፈልጋል።

የግብይት ስፍራዎችን መከታተል መቆጣጠርና ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪን ማስቀረት ይገባል።

አጠቃላይ የንግድ ስርዓቱ ጤናማነት መከታተል ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከሸገር ሲቲ ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ተሳታፊዎች በበኩላቸው በቅንጅት፣ በትብብርና በትኩረት በመስራት ህገ-ወጥነትን በመቆጣጠር የበዓል ግብይቱን ሰላማዊና የተረጋጋ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.