
የአዲስስ አበባ ንግድ ቢሮ ለትንሳኤ በዓል በቂ የምርት አቅርቦት በመፍጠር እንዲሁም ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር እተየሰራ መሆኑ ገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ለ2017 ዓ.ም ትንሳኤ በዓል በቂ የምርት አቅርቦትን በመፍጠር እንዲሁም ህገወጥ የንግድ አንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር የተረጋጋ ገበያ እንዲኖር የሚያስችሉ ተግባራት በትኩራት እየተሰራ መሆኑን ተገለፀ፡፡
የቢሮዉ ኃላፊ ወ/ሮ ሀበባ ሲራጂ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ቢሮዉ ለትንሳኤ በዓል በከተማዋ ምንም አይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በማድረግ ገበያዉን ለማረጋጋት የሚያሰችሉ ተግበራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የቢሮ ሃላፊዎ እንደገለፁት 210 የእሁድ ገበያዎች ፤ 4 የገበያ ማዕከላት፤ የተዘጋጁ ባዛሮች 15 ፤ ከቁም እንሰሳ ማዕከላት 5 ፤ በቂ አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች የተዘጋጀ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
ከቁም እንሰሳት ጋር በተያያዘም የህብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ የበግ፤ የፍየልና የደልጋ ከብቶችን አቅርቦት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
ማንኛውም ሕገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ወይዘሮ ሃቢባ ህብረተሰቡ በ8588 ነፃ ስልክ ጥሪ ላይ ጥቆማ እንዲሰጥ አስስበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.