
የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች 200 ሺህ ለሚሆኑ የኑሮ ጫና ላለባቸውና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋርተናል።
ማዕድ ማጋራት ለነዋሪዎቻችን ፍቅራችንን እና አክብሮታችንን የምንገልፅበት እዲሁም እርስበርስ መተሳሰብን የምናዳብርበት የሰዉ ተኮር እሳቤያችን ተግባራዊ ማሳያ ነዉ።
እንደ ሁልጊዜው ሁሉ ዛሬም ‘መስጠት አያጎድልም’ ብለው ከጎናችን የቆሙ የከተማችን ባለሃብቶችን፣ ተቋማትን እና ወጣት በጐ ፍቃደኞችን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
መልካም በዓል !
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.