.png)
በመዲናችን በሁሉም የግብይት ቦታዎች በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩ ተገለፀ
ለመጪው የትንሣኤ በዓል በመዲናችን በሁሉም የግብይት ቦታዎች በቂ የምርት አቅርቦት መኖሩ ተገልጿል።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የግብርና ምርቶች፣ እንስሳትና የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም ሌሎች ግብዓቶች በበቂ መጠን በከተማዋ ባሉ በሁሉም የግብይት ማዕከላት የቀረቡ በመሆኑ ኅብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኙ የገበያ ማዕከላት ምርቶቹን በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንደሚችል ተገልጿል።
በከተማችን የተረጋጋና ፍትሀዊ ግብይትን በዘላቂነት ለማስፈን ከማዕከል እስከ ወረዳ የተደራጀዉ ግብረሀይል በርካታ ዉጤታማ ስራዎችን እየሠራ እንደሚገኝና አሁንም አደረጃጀቱን በማስፋት በሁሉም የግብይት ቦታዎች የመስክ ድጋፍ ክትትልና ቁጥጥሩን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ሸማቹ ህብረተሰብ በግብይት ስርዓት ወቅት ህገወጥ ድርጊትን ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ ሀይሎች ሲያጋጥሙት በባለቤትነት በአቅራቢያቸዉ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት፣ ለደንብ ማስከበር ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮች፣ ለህገወጥ ንግድ ቁጥጥር ግብረ ሀይል እና በአካባቢዉ ለተደራጁ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጪ አካላት በመጠቆም ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
ይህ ቅንጅታዊ ስራ በከተማችን የተረጋጋና ፍትሀዊ የግብይት ስርዓት እንዲሠፍን እንዲሁም የህግ የበላይነት እንዲከበር ጉልህ ሚና ያለዉ መሆኑም ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.