የሀኖይ ጉባኤ አነስተኛ ቢሆኑም በሚገባ የተቀናጁ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የሀኖይ ጉባኤ አነስተኛ ቢሆኑም በሚገባ የተቀናጁ የፒ4ጂ ፕሮጀክቶች ትርጉም ያለው ውጤት እንደሚያስገኙ እና ለማሳደግም ትልቅ አቅም ያላቸው መሆናቸውን አሳይቷል።

ኢትዮጵያ በ2027 የሚካሄደውን አምስተኛውን የፒ4ጂ ጉባኤ ለማዘጋጀት ችቦውን በመረከቧ ኩራት ይሰማታል። ይኽን እድል በፅናት እና በቁርጠኝነት በመያዝ የቬይትናም፣ ኮሎምቢያ፣ ዴንማርክ እና የኮሪያ ሪፐብሊክን የታየውን ስኬታማ የዝግጅት ውርስ ጨምረን እናስቀጥላለን።

ትብብር፣ ፈጠራ፣ አካታችነት እና ተግባር በተባሉት የፒ4ጂ አስኳል መርሆዎች በመመራትም የኢትዮጵያ 2027 ጉባኤ በአረንጓዴ ኢንደስትሪ ልማት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ግብርና ብሎም ወጣቶችን እና ሴቶችን ማብቃትን የአረንጓዴ ሽግግር ወሳኝ አስፈፃሚ የማድረግ አስፈላጊነትን ትኩረት ሰጥቶ ይዘጋጃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
  https://linktr.ee/addisababacommunication


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.