ዛሬ 446 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች፣ ለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ 446 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች፣ ለሀገር ባለዉለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማችን ነዋሪዎች አስተላልፈናል።

በከተማችን ከህዝብ በምንሰበስበው ገቢ ከምናከናውናቸው ታላላቅ የልማት ስራዎች ጎን ለጎን በጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችን እና የተለያዩ ተቋማትን በማስተባበር የአቅመ ደካሞችን ኑሮ የሚያሻሽሉ ሰዉ ተኮር ስራዎችን እየሰራን የምንገኝ ሲሆን፣ በተለይ የተገፉ እና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት እድል ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎች እምባ ሲታበስ ማየት ደስታን ይሰጠናል።

ዛሬ ካስረከብናቸዉ 446 ቤቶች ዉስጥ በቦሌ ክፍለ ከተማ ጎላጎል አካባቢ የሚገኙትን ቤቶች ግንባታ ያገዙን የገቢዎች ሚኒስቴርን፣ የጉምሩክ ኮሚሽንን እና የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣንን እንዲሁም ሌሎች  በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶች እና ተቋማትን በራሴ እና በነዋሪዎቻችን ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.