
ዛሬ 446 ቤቶች በከተማችን ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እንዲሁም ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ የከተማችን ነዋሪዎች ተላልፈዋል::
በመድረኩ ላይ የተገኙት የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ባስተላለፉት መልዕክት ከለውጡ ወዲህ የመዲናችን አዲስ አበባን ገጽታ የቀየሩ፣ የነዋሪውን ህይወት በከፍተኛ ሁኔታ ያሻሻሉ እንዲሁም ከተጎሳቆለ አኗኗር ወደተሻለ ኑሮ የቀየሩ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል::
ይህ ሰው ተኮር ተግባር የመንግስታችን አቅጣጫ ሆኖ የቀጠለ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህንን ወደ ተግባር በመቀየር ውስጥ ከፍተኛ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሯ የገቢዎች ሚኒስቴር በዚህ ውስጥ ተሳትፎ በማድረጉ ታላቅ ደስታ የሚሰማው እና በቀጣይም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመሆን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም ገልጸዋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.