ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ አዲስ አበባን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹና ማራኪ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ተጠናክሮ ቀጥሏል።አቶ ጃንጥራር አባይ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማቱ ነዋሪውን የልማቱ ተሳታፊ በማድረግ ፕሮጀክቱ የሚሰራባቸውን የመንገድ ዳርቻ የወሰን ማስከበር ተግባር በወረዳ 05፣ 07 እና 08 የመንገድ ስራውን ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። 

የመንገድ ኮሪደር ፕሮጀክቱን የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ኢምባሲዎች፣ የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት የልማት አጋርነታቸውን በተግባር እያሳዩ ይገኛል። 

የመንገድ ኮሪደር ልማቱ ከተማዋን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ከማድረግ ባለፈ የስማርት ሲቲ ስታንዳርድን በማሟላት የከተማዋን ገጽታ በመቀየር የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አስተያየት ሰጭዎች ተናግረዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.