
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ 4ተኛ አመት 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን በ3 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
አጀንዳዎቹም ፦
1ኛ. ተቋርጦ የነበረዉ የመኖርያ ቤት ህብረት ሥራ ማህበራት አገልግሎትን ለማስቀጠል ተጠንቶ የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ ላይ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ሊፈታ በሚችል አግባብ የውሳኔ ሀሳብ አሳልፏል።
2ኛ. የብርሃን አይሰውራን፣ የመነን እና የገላን ቦርዲንግ ት/ቤቶች ካላቸው ልዩ ስምሪት፣ የጥራት ደረጃ እና ከሚያንቀሳቅሱት ሀብትና ንብረት አስተዳደር አንፃር ህጋዊ ሰውነት ኖሯቸው እንዲተዳደሩ እና ተጠሪነታቸው በቀጥታ ለከተማዉ ትምህርት ቢሮ እንዲሆን የቀረበዉን ደንብ መርምሮ አጽድቋል ::
3ኛ. ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ፕሮጀክቶች የቀረበ የመሬት ማስፋፊያ ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ተገቢነት ያለዉ መሆኑን በማረጋገጥ አጽድቋል::
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.