ዛሬ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ 25ኛው...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ 25ኛውን እና 26ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ከፍተን አገልግሎት አስጀምረናል።

ከ2014 ጀምረን በቀን አንድ ጊዜ እንኳን ምግብ ለማግኘት ለሚቸገሩ ወገኖቻችን 24 የምገባ ማዕከላትን ከፍተን ንፁህ፣ ጤናማ እና ትኩስ ምግብ ለአቅመ ደካሞች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ወገኖቻችን እየመገብን መሆናችን ይታወቃል።

 የትንሣኤን በዓል ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለከተማ ጉራራ አካባቢ 25 ኛውን እና በቦሌ ክፍለ ከተማ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ደግሞ 26 ኛውን የምገባ ማዕከል ከፍተን አገልግሎት አስጀምረናል።

ዛሬ ያስጀመርናቸዉ እነዚህ  የምገባ ማእከላት በተለያዩ የከተማችን አካባቢዎች በመጠለያ ይኖሩ የነበሩ እና ምንም ገቢ የሌላቸዉ አቅመ ደካሞች እና ለተለያዩ ለማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖቻችን ያሉበት አካባቢ በመሆኑ እነሱን ታሳቢ በማድረግ ነዉ ።

25ኛውን የምገባ ማዕከል የገነቡልን እንዲሁም የምገባውን ወጪ የሚሸፍኑልን የአያት አክሲዮን ማህበርን እና የኢፌዴሪ የጉምሩክ ኮሚሽንን በራሴ እና በተጠቃሚዎቹ ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ::
ጊዜያዊ ችግሮቻችንን በመረዳዳት እየተሻገርን ለዘላቂ ልማታችን ደግሞ 24/7 በመስራት የኢትዮጵያን ብልጽግና እናረጋግጣለን።

መልካም የትንሳኤ በዓል

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.